Saturday, 7 October 2017

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ለታዳሽ ኃይል ልማት አንድ ቢሊዮን ብር መደበ -ethiopianreporter

በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጀክቶች የአውሮፓ ኅብረት የአንድ ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ማክሰኞ መስከረም 23 ቀን 2010 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በተከፈተው የታዳሽ ኃይል ልማት ጉባዔ ንግግር ያደረጉት የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ዩሃን ቦርግስታም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የታዳሽ ኃይል ልማት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ልማት ዋና አካል አድርጎ መቅረፁን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው የኢንዱስትሪ ልማት የኃይል አቅርቦት ወሳኝ ሚና እንዳለው የገለጹት ሚስተር ቦርግስታም፣ መንግሥት ለታዳሽ ኃይል ልማት ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ 90 በመቶ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታመነጨው ከውኃ ኃይል ነው፡፡ የተለያዩ የንፋስ፣ የፀሐይና የጂኦተርማል ልማት ፕሮጀክቶች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ በአርዓያነት ልትጠቀስ የምትችል አገር ናት፤›› ብለዋል፡፡

Read More>>> 

No comments:

Post a Comment